Administration በኢንኩቤሽን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በኢንኩቤሽን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

30th June, 2025

በኢንኩቤሽን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ሰኔ 19/2017ዓ.ም

በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ በኢንኩበሽን አገልገሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውን የሰጡት ከስራና ክህሎት ቢሮ የዘርፉ ባለሙያዎች ሲሆኑ የኢንኩቤሽን አገልግሎት ጥቅሙን አስመልክቶ አገልግሎቱ ለሁሉም ማህበረሰብ አካላት እንደሚያሰፈልግ አስረድተዋል። የፈጠራ ሀሳብ ያለው የተማረም ያልተማረም ማንኛውም ሰው ሀሳቡ በልጽጎ ጥቅም ላይ ወደ ሚውል ሊቀየር እንደሚችል አስረድቷል። አያይዘውም የፈጠራ ሀሳብ ይዞ የሚመጡ የሀሳብ ባለቤቶችን በገለልተኛ አካል በማወዳደር በኮሌጁ ውስጥ በተቋቋመው ኢንኩቤሽን ማዕከል ለገበያ እስከሚደርሱ መደገፍ እንደሚገባ አስረድተዋል። 

የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን ዶክተር ጫላ ፈዬራ በበኩላቸው ባለሙያዎቹ ለሰጡት ማብራሪያ አመስግነው በአገልግሎቱ የተሰጠውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር በቀጣይ ኢንኩቤተሮችን ማስገባት እንደሚገባ ተናግረዋል። 

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ስልጠናው የነበረባቸውን ብዥታ እንዳጠፋላቸውና በቀጣይ የራሳቸውን የፈጠራ ሀሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር ግንዛቤ እንዳገኙ ተናግረዋል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with