Administration በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ'ወርቃማ ሰኞ' የአብሮነት እና የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሄደ።

በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ'ወርቃማ ሰኞ' የአብሮነት እና የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሄደ።

01st September, 2025

በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ'ወርቃማ  ሰኞ' የአብሮነት እና የልምድ ልውውጥ መርሀግብር ተካሄደ።

    ሰኞ : ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም

የመርሀግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን #ዶ/ር አሸብር ተክሌ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት እና የእውቀት ሽግግር መድረክ እያካሄደን እንገኛለን። በዚህ ደግሞ ብዙ ልምዶች ተገኝተዋል በማለት የገለጹ ሲሆን አያይዘውም ይህ የወርቃማው ሰኞ የአብሮነት መድረክ በየሳምንቱ ሰኞ ሰኞ  ለአጭር ደቂቃ እንደሚቀጥል በማሳወቅ ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኛ ያለውን ሀሳብ; እውቀት እና ልምድ  ለማህበረሰቡ ማካፈል የሚችልበት መድረክ መሆኑን ገልፆዋል ፡፡

በመቀጠልም ወርቃማ ሀሳቦቻችንን በወርቃማ ሰኞ በሚል የኮሌጁ የተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን #ወ/ሮ ዚነት ሰይድ <<ለውጥን ማስተዳደር>> በሚል ርዕስ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ተቋማዊ ለውጥ ማለት አንድ ተቋም ወይም ድርጅት ከለውጡ በፊት የነበረውን አደረጃጀት፣ አሰራርና የሰው ኃይል አቅም በለውጥ ሂደት ወደሚፈለገው አዲስ የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የሰው ኃይል አቅም ደረጃ ላይ ማድረስ የሚያስችል የማያቋርጥ ሂደት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ተቋማዊ ለውጥ ተልዕኮን በቅልጥፍናና በውጤታማነት ለመፈጸም፣ የተገልጋዮች/ደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት፣ ተወዳዳሪ ለመሆንና የተቋምን ህልውናን ለመጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል ።

        ጎኢኮ ኮሚኒኬሽን !!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with