Administration የወርቃማ ሰኞ መርሐግብር በተቋሙ ተካሄደ ።

የወርቃማ ሰኞ መርሐግብር በተቋሙ ተካሄደ ።

24th August, 2025

የወርቃማ ሰኞ መርሐግብር በተቋሙ ተካሄደ ።

         

       ሰኞ :ነሐሴ 12 ቀን /2017ዓ.ም

በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የወርቃማ ሰኞ መርሀግብር ተካሄደ ።በባለፈው ሳምንት በኮሌጁ የተጀመረው የወርቃማ ሰኞ ትግበራ ልምምድ በዛሬ እለትም ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ተካሄደዋል ።

መረሃ ግብሩ ላይ ተገኝቶ ሰራተኞችን ያወያዩት የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን  #ዶ/ር ጫላ ፋዬራ #'የስኬት አልፋና ኦሜጋ' በሚለው ላይ ገለፃ በማድረግ በተቋሙ ብቻ ሳይሆን በእለታዊ ኑሯችን ጭምር እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ካብራሩ በኋላ የስኬት ሳንካዎች የሆኑትንን በማብራራት እነዚህን ሳንካዎች እንዴት ማስወገድና ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ገለጻ አድርጓል።

በመጨረሻም የተጀመረው የወርቃማው ሰኞ ልምምድ  የተቋሙን ራዕይ ከማሳካትም በተጨማሪ አዳዲስ እሳቤዎች እንዲበለፅጉ እድል የሚፈጠረው መሆኑን ተገልጿል ።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with