የኮሌጁ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ
ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ግምገማ ተካሄደ፡፡
በቀረበው ሪፖርት እንደ ተብራራው በበጀት ዓመቱ የተለያዩ በተቋሙ የተሰሩ ፕሮጀክቶች ፣ዲጂታላይዜሽ ሥራዎች፣ ከባለድረሻ አካለት አና ከኢንዱስትሪዎች ጋር የተሠሩ ሥራዎች፣ የሰልጣኝ ምዘና የ ተጠኑ ጥናቶች ፣ ለ2018 የሰልጣኞች ቅበላ በተመለከተ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ስለተደረገ ውይይት፣ የዓመቱ የስልጠና ሂደት፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አተገባበር አስመልክቶ ከሁሉም ዘርፍ አመራሮች ለተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡
በተለይም ኮሌጁ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ የISO 21001:2018 ወደ ትግበራ መግባቱንና ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ በአንድነት የራሱ አስተዋጽኦ ስላደረገ ውጤት መምጣቱ ተብራርተዋል፡፡
በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀጣይ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ መሟላት ያለባቸው ግብዓቶችና መተግበር የሚኖርባቸው አሰራሮች ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቷል።
በሌላ በኩል የውስጥ ገብ ከማሳደግ አንፃር በኮሌጁ የሚተዳደር 'ጎፋ ዩኒት ማኑፋክቸሪንግ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር' የተለያዩ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት በአቶ ይታያል ማብራተ በአመቱ ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ለታዳሚው አቅርቧል
በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት በጠንካራ ጎን የታየው እንድቀጥል እና ክፍተት የታዩባቸው አፈፃፀም ደግሞ በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ እንድካተት በመስማማት መድረክ ተጠናቋል፡፡