Home የወረዳው ስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ከጎፋ ኢንዱስትራል ኮሌጅ ጋር በጋራ በመሆን የልል ስልጠና ሰጠ።

የወረዳው ስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ከጎፋ ኢንዱስትራል ኮሌጅ ጋር በጋራ በመሆን የልል ስልጠና ሰጠ።

11th July, 2025

የወረዳው ስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ከጎፋ ኢንዱስትራል ኮሌጅ ጋር በጋራ በመሆን ለወረዳው ወጣቶችና የስራ  ፈላጊዎች የልል ስልጠና ሰጠ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በ90 ቀናት እቅዳችን የስራ ዕድል ንቅናቄ ስራዎች ለማጠናከር የልል እና የቴክኒክ ስልጠናዎች ለስራ ፈላጊዎች ለመስጠት የታቀደ ሲሆን በ2018 በዝግጅት ምዕራፍ ለ1072 ስራ ፈላጊዎች የልል አንደኛ ዙር ስልጠና መሰጠቱን የወረዳው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ሽታ ገልጸዋል። 

ጨምረውም ቀጣይ የቴክኒክ ስልጠና  240 ስራ ፈላጊዎች ጎፋ ቴክኒክና ሙያ ድረስ በመሄድ እንዲሰለጥኑ ይደረጋል ያሉ ሲሆን መንግስት ከሚያቀርባቸው ግብዓቶች በተጨማሪ የስራ  አመራረጥ  ችግሮች በስራ ፈላጊዎች በመኖሩ የሚሰጡ ስልጠናዎች በአመለካከት ግንዛቤ መስጠት አስፈላጊ መሆኑዠ አንስተዋል። 

አክሎም ስራ ዕድል ፈላጊዎች ድጋፍና ስልጠና ከተሰጠ ውጤታማና አምራች ዜጋ እና ክህሎት መርህ ስራ እድል ፈጠራ መፍጠር እንችላለን በለዋል።

 በወረዳው በሁሉም ቀጠና ግንዛቤ መሰጠቱን ገልፆ ቀጣይ እንደ ወረዳ ማንኛውም ስራ ፈላጊዎች ስራ ዕድል ከመፍጠራቸው በፊት ስልጠና እና ግንዛቤ መውሰድ እንደሚገባቸው በመናገር ይህ ስሆን ራሳቸውን በመጥቀም አገራቸውን መጥቀም እንዲሁም ለሌሎችም ስራ ዕድል መፍጠር ይችላሉ በማለት ገልፀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with